የእኛ የኢትዮጵያውያን አዲሱ ዓመት፣ 2018፣ በደጅ ነው። አዲሱን ዓመት እንዴት እንቀበለው? 2018ን ስናስብ ከሚሰማን እንጀመር። ለአፍታ ያህል ሀሳባችንን ተወት አድርገን አካላችንን ለማድመጥ እንሞክር። አካላችን ምን ሹክ አለን? ሰውነታችን ውጥር ጥብብ ሲል ተሰማን ወይስ ተፍታታ?
አብይ የሆኑ አመለካከቶች
አዲሱ ዓመት አጠባበቅ ተቃርኖ ሊባሉ የሚችሉ ሁለት ዕይታዎችን ይንጸባረቁበታል። የመጀመሪያው የሚመጣው ዓመት በጎ ይጎላበታል ባይና እየጨመረ የሚሄድ ንጋትን ጠባቂ ነው። ነገ የበለጠ ይሠምራል ብሎም ያምናል። የከበበን የዛሬው የፍትህ መታጣት፣ ሌብነት፣ መገፋፋት፣ የከበበን ሥጋት፣ በልማት ስም የሚፈናቀሉ ሰዎች እንባ፣ በየቀኑ የሚፈሰው የንጹሀን ደምስ ሲባል መልሱ እኚህ ሁሉ በነገው በጎነት ይሸነፋሉ ነው። አተያዩ የዛሬ ክፋት ከነገ ጋር ስላለው ትሥሥር አምብዛም አይጨነቅም፤ “ድንገቴ በረከት” ጠባቂነት ይጎላበታል። የድንገቴ በረከት አጠባበቁም በተቺዎቹ መንገዱን የተላሎች ወይም የየዋሆች ተብሎ እንዲፈረጅ ያደርገዋል።
ሁለተኛው አጠባበቅ ክፋት ነገ ላይ ከዛሬ ይልቅ ይበልጥ እንደሚጨምር ይጠብቃል፤ ጨለማው ይበረታል የሚል ድምጸት ይጎላበታል። ሌሎች የሚጠቅሱዋቸው የመንገዶች ስፋት፣ በየመንገዱ እና በየለሊቱ ብቻውን የሚንቦገበገው ብርሃን፣ በየጊዜው የሚመረቁት እና የሚጀመሩት የብዙ ቢሊዬኖች ፕሮጀክቶች ዐይኖቻቸው አይገቡላቸውም። እኚህ ሁሉ መሠረተ ልማቶች ከሰው ልማት አንጻር እዚህ ግቡ የሚባሉ አይደሉም ብለው ይተቹዋቸዋል። ስለ ክፋት መጨመርም መረጃ ብቻ ሳይሆን ማስረጃዎቹን ሰንደዋል፣ በብዙ መልኩ የተጀመረው የአዝቅት ጉዞ ይበልጥ አቆልቁሎ ይታያቸዋል። አተያዩም በአዎንታውያኑ ጨለምተኛ በሚል ይፈረጃል።
የዚህ አሰላስሎ አላማ እነዚህን አተያዮች ማስታረቅ፣ መሞገት፣ ወይም ማሞገስ አይደለም። ጥያቄው ከነዚህ ሁለት ገዢ ቅኝቶች የሚሻል ሌላ አማራጭ አለን ነው። ክፋትን ሳይክዱና የእኛን አድራጊነት ሳያንኳስሱ ተስፋ ማድረግ ይቻላል የሚለውን ይጠይቃል። በተለይ ደግሞ በእግዚአብሔር የምናምን እና ከዚሁ እምነታችንም የተለየ ጥንካሬ እና አይበገሬነትን የምንቀናጅ ከሁለቱ ገዢ ቅኝቶች የተለየ አተያይ እና አኗኗርን መከተል እንችላለን? የአሰላስሎው ዓላማ ሕይወታችንን ሆነ የሚቀጥለውን ዓመት አጠባበቃችንን በብዙ ክህደት እና ተላላነት ታጅቧል ተብሎ ከሚከሰሰው ሆነ ምንም የተስፋ ፍንጣቂ መመልከት ከሚቸገረውና በጨለምተኝነት ከሚከሰሰው አስተሳሰብ በተሻለ መልኩ ልንቃኝበት የምንችለውን ሦሥተኛ አማራጭን ለመጠቆም ነው።
የጌታ ቅርብነት
ሦስተኛው የዘመን አጠባበቅ መንገድ የጌታን ቅርብነት በመገንዘብ እና በመለማመድ ላይ የተመሠረተ ነው። አተያዩ ምንም ነገር ከማሰቡ በፊት የጌታን ቅርብነት በማስታወስ ይጀምራል። በጌታ ቅርብነት መቃኘት ደግሞ ብዙ ነገርን ይለውጣል። የከበበንን ክፋት ሳንክድ በተስፋ መኖር እንድንችል ያግዘናል። ተስፋ ለማድረግ በሚል ግን ያለንበት ዓለም የማስጨነቁን ልክ አንክድም፤ የእኛንም ሚናም አናንኳስስም። የከበቡንን ማስጨነቆችንም ከሌሎች የበለጠ ተገንዝበንም ተስፋ ማድረጋችንን እንቀጥላለን። ሰላም ባጣ ዓለም እየኖርን ሰላማችንን መጠበቅ እንችላለን እንላለን። የሚታየው ክፋት ልባችንን እና ሀሳባችንን እንዲጎትትና ተስፋ ወደ መቁረጥ እንዲወስደንም አንፈቅም። እንዲህ ዓይነቱ መንገድ ግን ይቻላልን?
ለሦስተኛ አተያይ መነሾ የሚሆነን ምንባብም ፊሊጲሲዮስ 4፡6-7 ነው። ክፍሉ “ ጌታ ቅርብ ነው። በነገር ሁሉ በጸሎትና በምልጃ ከምስጋና ጋር በእግዚአብሔር ዘንድ ልመናችሁን አስታውቁ እንጂ በአንዳች አትጨነቁ። አእምሮንም ሁሉ የሚያልፍ የእግዚአብሔር ሰላም ልባችሁንና አሳባችሁን በክርስቶስ ኢየሱስ ይጠብቃል።” ይለናል። ክፍሉ የሚቃረኑ በሚባሉ ሁለት ውጥረቶች የተያዘ ነው፤ ስለመጨነቅ እና ስለ ሰላም ያሳስበናል።
አንዳንድ የሕይወት ገጠመኞች በእርግጥም ክፉዎች ናቸው። ብቻችንን የቀረን ያክል እንዲሰማን ያደርጋሉ። ፍጥረቱን በቸርነቱ የሚያስገባ የሚያስወጣ አምላክ እኛን ከመግቦቱ ያጎደለን ስሜት ይፈጥሩብናል። በሕይወታችን ለዘመናት የተለማመድነውን በጎነት በጥርጥር እንድናይ የሆነው ግን ወደን አይደለም። የደረሰብን ክፉ ነገር ህልውናውን እንድንክድ ባያደርገንም እንኳን የሁሌውን የደግነት አብሮነቱን በመተማመን እንዳንጠብቅ ያደርገናል። እንደመዝሙረኛው “አምላኬ ለምን ተውኽኝ? እኔን ከማዳንና ከጩኽቴ ቃል ሩቅ ነህ።” (መዝ 22፤1) ስንልም እንገኛለን። እግዚአብሔር እንደተወን ይሰማናል፤ ለአድነኝ ጥሪያችን ሩቅ ሆኖ ይታየናል።
ሰው ነንና ማናችንም የሚዘልቅ ብቸኝነትን አንወደውም እና ሁኔታዎች ገፍተው ያደረሱን የብቸኝነት ጊዜያት ይረብሹናል። ከብቸኝነቶች ሁሉ የከፋው የብቸኝነት ስሜት ደግሞ የሁሉ ረዳት የሆነው አምላክ ብቻችን እንደተወን ወይም በጠላትነት እንደተነሳብን ሲሰማን ነው። ይኽንን ስሜት መዝሙረኛው (51፤11) ሲያስተናግድ “ከፊትህ አትጣለኝ፤ ቅዱስ መንፈስህንም ከእኔ ላይ አትውሰድብኝ።” ሲል ተማጥኗል። የእግዚአብሔርን ቅርብነት በሕይወቱ የተለማመደ ሰው ደግሞ ከፊቱ መጣልን አይፈልግም።
በአምላክ የመተው ስሜት ከአሉታዊ ስሜቶቹ ሁሉ እጅጉን የሚያስፈራው ነው። ስለዚህም በእምነት የተሞላ ጸሎት ነው ብለን ባንኮራበትም እንኳን ራሳችንን አበረታተን ተውከን ያልነውን አምላክን መልሰን አትራቅ እያልን እንማጠነዋለን። “ጭንቀት ቀርባለችና የሚረዳኝም የለምና ከእኔ አትራቅ።” ብለን እንዲያድነን እንጠራዋለን (መዝ 22 11)። አምላክ ርቆናል የሚለውን ስሜትም በታገለን ቁጥርም “አንተ ግን አቤቱ ከእኔ አትራቅ፣ አንተ ጉልበቴ እኔን ለመርዳት ፍጠን” (ቁ.19) ብለንም እንጮኻለን። የሚያዋጣው መንገድ በእርግጥም ይኼኛው መንገድ ነው።
በውጥረት ውስጥ የጌታን ቅርብነት ማስታወስ
ስጋት ሲከበን እና ጭንቀት ሲቀርበን ምን እናስታውስ? የሚያስጨንቀንን ነገር ሳንተው ከመጠን በላይ ከመብሰልሰል እና ከስሜታዊ አሉታዊነት ራሳችንን እንዴት እንጠብቅ? “አይቻልም” ብቻ ከሚሰብከን ስሜትስ እንዴት ነጻ እንወጣ? ሐዋርያው በነዚህ ውጥረቶች ውስጥ አንድ ነገር እንዳንዘነጋ ያሳስበናል፤ እርሱም የጌታ ቅርብነት ነው። በጭንቀት መሃል የጌታን ቅርብነት ለራሳችን ሁል ጊዜ ከማሳሰብ መዘናጋት የለብንም።
የጌታን ቅርብነት ማሰብ የጌታን አብሮነት እና ብቻችንን አለመሆናችንን መረዳት ነው። በሁሉ ነገር ውስጥ ከጌታ አብሮነት ጋር መሆናችንን መገንዘብ አዲስ ኃይል ያስታጥቀናል። ከምንም በፊት ሁኔታዎች እያጎሉብን ከሚሰማን የተጣለ እና የተተወ ስሜት መንግለው ያወጡናል። የሰራን ጌታ፣ የሚጠነቀቅልን እና የሚንከባከበን መሆኑንም ልብም እንላለን። እግዚአብሔር ከእኛ ጋር እንደሆነ ያመንን ቀን በእርግጥም ምንም ነገር አያስፈራንም።
በእግዚአብሔር አብሮነት ውስጥ የተለምዶው ፍርሀት የመሸሹ ምክንያት ግልጽ ነው። ነቢዩ እንደሚል የእግዚአብሔር አብሮነት ፍርሃታችንን ያስጠንግጠዋል፣ ድንጋጤያችን በመረጋጋት ይቀይራል፣ ድካማችን ይታገዛል፤ በመደገፋችንም እንበረታለን። ጌታ ቅርብ ነው ማለት በእርግጥም “አትፍራ፤ እኔ አምላክህ ነኝና አትደንግጥ፤ አበረታሃለሁ፥ እረዳህማለሁ፥ በጽድቄም ቀኝ ደግፌ እይዝሃለሁ።” መባል ነው (ኢሳ 41፤10)። የእኛስ ምኞት በአምላክ መደገፍ አይደለምን?
የጌታን ቅርብነት ማወቅ ብቻችንን እንዳልሆንን እንዲሰማን ያደርጋል። የምንደገፍበት ትከሻ የማይሰበር ሸንበቆ መሆኑን ስለምናውቅም እንረጋጋለን።
የጌታን አብሮነት መለማመድ
የጌታ ቅርብነት የሚሰጠን ሌላኛው መተማመን የምናወራውን ነገር ጌታ እንደሚሰማን ማወቅ ነው። ስለዚህም ነገራችንን ሁሉ፣ አንዳችን ሳናስቀር፣ ፊቱ በዝርዝር እንድናቀርብ አቅም ይሰጠናል። ስንናገርም፣ የሚያስፈልገንን ስናሳውቅም፣ እየሰማን እንደሆነ እርግጠኞች እንሆናለን። በሌላ አነጋገር አምላክ ቅርባችን ነው ማለት አምላክ አለ ማለት ብቻ አይደለም አምላክ አለልኝም ማለት ነው። የአምላክን ቅርብነት አዕምሮአዊ እውቀት ብቻ ስላልሆነም ልባችንን በፊቱ እናፈሳለን። በጸሎት፣ በልመና እና በምስጋና ም በፊቱ ራሳችንን እናቀርባለን።አብሮነቱን ማወቅ ኑሮዋችን የሚያስጨንቀንን የማሳወቅ እንጂ የመሳቀቅ እንዳይሆን ያደርገዋል።
ለጌታ ማሳወቅ ማለት ግን አንዳንዶቻችን እንደምናስበው ጌታን ማዘዝ አይደለም። የጌታን ቅርብነት ማወቅ ሁሉን ነገር በፊቱ ማምጣት እና በተጨነቅንበት ነገረ ጉዳዩ ላይ መሪነቱን ለእርሱ መተው ነው። ሁሉን በሚችል እና በሚያውቅ አምላክ ፊት ተገኝቶ መሪውን ካልጨበጥኩ ማለትስ እንዴት ልክ ሊሆን ይችላል? ከእኛ በጎ ሀሳቦች ይልቅ የእርሱ ደካማ የሚመስሉ መንገዶችስ በብዙ እጥፍ አይሻሉምን? በእርግጥም ከሰው ጥበብ ይልቅ የአምላክ ሞኝነት እጅጉን ይጠበባል (1ኛ ቆሮ 1፡25)።
ጸሎት ጉዳዬን ማስፈጸሚያ ነው የሚለው የተንጋደደ አስተሳሰብ ካልተሰተካከልን ግን ከጸሎት ብዙ አናተርፍም። ጸሎት የምንፈልገውን ነገር ከምናገኝበት መሳሪያነት ይልቅ ተደጋፊነታችንን ማስታወሻ መሆኑን፤ ከመናገር ይልቅ ማድመጥ እነደሚሻና ማሸነፊያ ሳይሆን በፈቃዱ መሸነፊያ ቦታነቱን ከሁሉ በፊት መረዳት ይገባናል። ጸሎት ጥያቄያችንን እኛ በፈለግነው መልኩ ማስመለስ ሳይሆን አምላካችን ለእኛ ያለውን ፈቃድ መገንዘቢያና ለፈቃዱም ፀጋ መጎናጸፊያ መሆኑን እንረዳ። በጸሎት ውስጥ የማይነጥፈው አቅርቦቱ ፀጋ ነው፤ ጸጋውም ሁሌ አሸናፊዎች ያደርገናል፤ በሰው ስሌት ታንፋችኋል እየተባልንም አሸናፊ ከተባሉት ሁሉ የበለጥን አሸናፊዎች እንሆናለን።
በጸሎት ውስጥ የምናገኘው የጸጋው አቅርቦት ግን ከምናስበው እና ከምንጠብቀውም በመጠንም ሆነ በይዘት ሊለይ እንደሚችልም ማስታወስ ይበጀናል። በፊቱ በመቅረብ ውስጥ የምንፈልገውን ነገር ሁሉ እንደምናገኝ የተሰጠን ዋስትና የለም። የምንፈልገውን ነገር ያላገኘነውም አምላካችን ንፉግ ስለሆነ አይደለም። የፈለግነውን ነገር ያጣነው ከአምላክ ንፉግነት አንጻር ቢሆንማ ኖሮ በምናልፍበት ነገር ውስጥ የሚያስፈልገንን ጸጋንም ባላገኘንም ነበር::
በነውጥ መካከል ከበጎነቱ እንካችሁ ተብለን የተሰጠን ሰላማችንም የተደገፍነው ጌታ የሚረዳ እና የሚያግዝ ደግሞም ከሁሉ በላይ የሚያስፈልገንን ከእኛ በላይ የሚያውቅ መሆኑን ከመረዳት ይመነጫል። የእግዚአብሔር ሰላም በክርስቶስ ኢየሱስ ልባችንን እና አሳባችንን ይጠብቃል። በክርስቶስ ኢየሱስ በኩል የምናገኘው የሰላም ዓይነት አዕምሮን የሚያልፍ ነው።
አእምሮን የሚያልፍ ሰላም
በአብሮነቱ ውስጥ የምንቀዳው ሰላም ለምን አእምሮን የሚያልፍ ተባለ? አእምሮን የሚያልፍ ሰላም መገለጫው ምንድን ነው? አእምሮን የሚያልፍ ያሰኘው የእኛ የእጅ ሥራ አለመሆኑ ነው። ሰላሙ የምንቀበለው እንጂ የምንሠራው አይደለም። ለዚህም ነው መቋጫው መታበይና መኩራራት ሳይሆን የምስጋና ልብ የሚሆነው። በመገኘቱ ውስጥ እየተለማመድነው ያለነውን ሰላማችንን እንኳን እኛም ጭምር የማንረዳበት ጊዜ አለ። በስጦታ መገኘቱ ያገኘነው ሰላም አእምሮን የሚያልፍ ያሰኘው ሰዋዊ ማብራሪያ ስለሌለው ነው። ሰላሙ ከሰላም አለቃ “እንካችሁ” የምንባለው መለኮታዊ ስጦታ ነው።
አእምሮን የሚያልፍ ሰላም የጌታን ንግግር ያስታውሰናል፤ ሰላሙም የጌታ ሰላም ነው። የሚሰጠንም እርሱ ነው። ሰላሙም ዓለም የሚሰጠው ዓይነት አይደለም። መለያውና ምንጩም ዘላቂነቱ ነው። የተፈጻሚነቱ ዋስትና ራሱ እግዚአብሔር ነው። በሁኔታዎች ላይ የተመሰረተ አይደለምና አይናወጥም። በማግኘትና በማጣት ውስጥ አይነቀነቅም። የሚገኘውም ሁሉን ነገር ለእርሱ አሳልፎ በመስጠት ውስጥ ነው።
ልባችንና ሃሳባችን በነውጦች መካከል እንዳይበታተን የሆነበት ዋነኛ ምክንያት የእርሱ ቅርበትና አብሮነት ነው። አብሮነቱ ልባችንንና ሃሳባችንን ለየቅል የሚያሮጥ አይደለም። አንዳንዴ እንደምንሆነው ሃሳባችንን አሸንፎ ልባችን ግን የሚሸነፍበት አይደለም። ልባችንና ሃሳባችን በስምረት በመገኘቱ ስለሚደገፍ አይናወጥም። ይህም በነውጥ ዓለም በእግዚአብሔር ላይ በመደገፍ ተስፋን እንድናደርግ ያስችለናል። ሦስተኛው መንገድ በእርግጥም የአምላክን ቅርብነት የማወቅ፣ የሚያስጨንቀንን ነገር ሁሉ የማሳወቅ፣ ሰላምን ከሰላም አለቃ እንደ መለኮታዊ ስጦታ የመቀበል መንገድ ነው። አዲሱ ዓመትም የእግዚአብሔርን ቅርብነት የምናስታውስበትና በመገኘቱ የምንኖርበት ዓመት እንዲሆን ምኞቴም ጸሎቴም ነው።
_
ዶ/ር ተካልኝ ነጋ አንጎሬ
Research Center
ፈጣን በሆነውና ፉክክሩ ባየለበት የቢዝነስ ዓለም ውስጥ፣ መሪዎች ስኬታቸውን ሙሉ በሙሉ በቁሳዊ ዕድገት፣ በትርፍ ጭማሪና ከገበያው ባላቸው ድርሻ ላይ ብቻ ተመሥርተው በመለካት ሊጠመዱ ይችላሉ። እንደ ክርስቲያን የቢዝነስ መሪዎች ግን፣ የበለጠ ዐደራ አለብን፤ የበለጠ መስፈርት አለን። መስፈርቱም፣ “የቢዝነስ መሪነታችን ከእግዚአብሔር መንግሥት መለኪያዎች ጋር የሚስማማ ነው ወይስ አይደለም?” የሚለው ነው። በእግዚአብሔር ፊት ስኬት ማለት ሰፊ የቢዝነስ “መንግሥት” መገንባት አይደለም፤ ይልቁንም የምንገነባውን ነገር የቱንም ያህል ቢሆን የገነባነው ዘላለምን እያሰብን ነው ወይ የሚለው ነው።
አንድን ክርስቲያን የቢዝነስ መሪ ወደ ዘላቂና ዓላማ ተኮር ስኬት የሚመሩ ዐሥር መርሖዎችን አብረን እንመልከት።
1. ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ራእይ
ስኬታማ ክርስቲያን የቢዝነስ መሪ የሚሠራውን ነገር የሚሠራው ዘላለምን እያሰበ ነው። የቢዝነስ ግቦቹን እግዚአብሔር ለሕይወቱ ካለው ዓላማ ጋር አብሮ ያስኬዳል። ዕቅዶቻችንን ለእግዚአብሔር ስናስገዛና ለእርሱ ዐደራ ስንሰጥ፣ ዐላማችንን ያጸናል።
“የምታደርገውን ሁሉ ለእግዚአብሔር ዐደራ ስጥ፤ ዕቅድህም ሁሉ ይሳካልሃል።” (ምሳሌ 16፥3)
2. ከሁሉ በላይ ሐቀኝነትን ማስቀደም
ቢዝነስም ሆነ የትኛውንም የምናደርገውን ነገር በሐቀኝነት ማከናወን፣ ገንዘብ ሊገዛቸው የማይችሉ ዕድሎችን ይፈጥራል፤ በገንዘብ ኃይል ሊከፈቱ የማይችሉ በሮችን ይከፍታል። እግዚአብሔር በቢዝነሳቸውም ሆነ በሕይወታቸው ቀጥተኛውን መንገድ የሚከተሉትን ያከብራቸዋል።
“መልካም ስም ከብዙ ብልጽግና ይመረጣል፤ መከበርም ከብርና ከወርቅ ይበልጣል።” (ምሳሌ 22፥1)
3. በጸሎት የታጀበ መሪነት
ክርስቲያን የቢዝነስ መሪ ያለመታከት የእግዚአብሔርን ጥበብ በጸሎት መሻት አለበት። የሚመራበት መንገድ ግልጽ እንዲሆንና የልብ መሰጠት እንዲኖረው መጸለይ ያስፈልገዋል። ኢየሱስ መጸለይ ከኖረበት፣ እኛማ የቱን ያህል ይበልጡን ጸሎት ያስፈልገን ይሆን?
“ኢየሱስ ግን ብዙ ጊዜ ወደ ገለልተኛ ስፍራ ወጥቶ ይጸልይ ነበር።” (ሉቃስ 5፥16)
4. የአገልጋይ ልብ መያዝ
እውነተኛ ታላቅነት የሚገኘው ሌሎችን በማገልገል እንጂ በመገልገል ውስጥ አይደለም። ክርስቶስ ምሳሌ ሆኖ ያሳየን መሪነት ከሥልጣንና ከማዕረግ ይልቅ ሰዎችን የሚያስቀድምና ለሰዎች ዋጋ የሚሰጥ ነው።
“ከእናንተ ትልቅ መሆን የሚፈልግ አገልጋያችሁ ይሁን...” (ማቴዎስ 20፥26)
5. የሥራ ልቀትን እንደ አንድ አምልኮ መቊጠር
በልቀት የተከናወነ ሥራ እግዚአብሔርን ያስከብራል፤ የእርሱ ባሕርይ ማሳያ ጠብታ ተደርጎ ሊታይም ይችላል። በቢዝነሳችን የምናደርገው ነገር ሁሉ፣ እንደ አምልኮ የምናቀርበው መሥዋዕታችን ሊሆን ይገባል።
“የምታደርጉትን ሁሉ ለሰው ሳይሆን ለጌታ እንደምታደርጉት ቈጥራችሁ በሙሉ ልባችሁ አድርጉት…” (ቈላስይስ 3፥23)
6. የእግዚአብሔርን መንግሥት ታሳቢ ያደረገ ባለዐደራነት
እንደ አማኝ የቢዝነስ መሪዎች፣ ለቢዝነስ የምንጠቀምበት ንዋይም ሆነ ልዩ ልዩ ግብዓቶች የተሰጡን የእግዚአብሔርን ዓላማ ለማስፈጸሚያ እንዲውሉ እንጂ ለግል ጥቅማችን ሲባል አለመሆኑን ማሰብ አለብን። ሁሉም በዐደራ የተሰጡን ናቸው። ታማኝ ባለዐደራ ደግሞ ከትርፍ ባሻገር ስለሚፈጥረው ተጽዕኖ ያስባል።
“ባለዐደራዎችም ታማኝ ሆነው መገኘት አለባቸው።” (1ኛ ቆሮንቶስ 4፥2)
7. ሰዎችን ማሳደግና ማብቃት
ሌሎች መሪዎችን ማስነሣት፣ እንዲሁም በብቃት መምራት እንዲችሉ ማስታጠቅ፣ ክርስቶስ መንግሥቱን ለመገንባት የተጠቀመውን አካሄድ የሚያንጸባርቅ መንገድ ነው። ጠንካራ የሆነና መሪዎችን የሚያበቃ የጋራ ሥራ ተጽዕኖን ለማስፋት ሁነኛ ዘዴ ነው።
“ይኸውም የክርስቶስ አካል ይገነባ ዘንድ፣ ቅዱሳንን ለአገልግሎት ሥራ ለማዘጋጀት...” (ኤፌሶን 4፥12)
8. ጥበብ የተሞላ ምክርን መስማት
እግዚአብሔር ብዙ ጊዜ በእርሱ መንፈስ በተቃኙ አማካሪዎችን አልፎ ይናገራል። ውሳኔዎቻችን በብዙ የታመኑ አማካሪዎች የተደገፉ ሲሆኑ ስኬትን የመቀዳጀት ዕድላችን ይጨምራል።
“ምክር ሲጓደል ዕቅድ ይፋለሳል፤ በብዙ አማካሪዎች ግን ይሳካል።” (ምሳሌ 15፥22)
9. ለብቻ የመቆም ድፍረት
አንዳንዴ ሐቀኝነት ሲፈተን፣ ክርስቲያን የቢዝነስ መሪዎች ጎርፉ ከሚፈስበት አቅጣጫ በተቃራኒው ጸንተው መቆም የሚጠበቅባቸው ሁኔታ ይፈጠራል። እንዲህ ያለው ድፍረት ወይም ጀግንነት የሚመነጨው ደግሞ ከእምነት እንጂ በብዙዎች ከመወደድ አይደለም።
“ንቁ፤ በእምነት ጽኑ፤ በርቱ፤ ጠንክሩ።” (1ኛ ቆሮንቶስ 16፥13)
10. አመስጋኝ እና ለጋስ መሆን
ስለሆነለት ነገር የሚያመሰግን ልብ የለጋስነት ሕይወትን የሚኖር ነው። ለጋስነት ደግሞ የበለጠ በረከትን ለመቀበል በር ይከፍታል። እኛም ለሌሎች በረከት መሆን እንችል ዘንድ እግዚአብሔር ያበለጽገናል።
“ሁልጊዜ በልግስና መስጠት እንድትችሉ በሁሉ ነገር ያበለጽጋችኋል...” (2ኛ ቆሮንቶስ 9፥11)
_
በመሪነታችን እግዚአብሔርን ለማክበር ስንነሣ፣ እነዚህ ዐሥር ቁልፍ መለያዎች ቢዝነስን በእምነት፣ በሐቀኝነትና ዘላለማዊ ራእይን በመሰነቅ እንድንፈጽም እንዲረዱን ጸሎቴ ነው። እውነተኛ ስኬት የሚገኘው ምን ተቀዳጀን በሚለው ብቻ ሳይሆን፣ ይበልጥ እንደውም ማንና እንዴት አገለገልን በሚለው ውስጥ ነው። እንዲህ ባለ ስኬት የምትሰማሩበት ሳምንት እንዲኖራችሁ ባረኳችሁ!
ፓ/ር ፍጹም ንጉሤ (አገልጋይ መሪ)
Scripture Focus:
"And when they had assembled with the elders and taken counsel, they gave a sufficient sum of money to the soldiers and said, 'Tell people, "His disciples came by night and stole Him away while we were asleep."’... So they took the money and did as they were directed." *(Matthew 28:12-15, ESV)*
1. The World’s Transaction: Paying to Hide the Truth
The religious leaders saw Jesus’ resurrection as a threat to their power and influence. Their response? A financial transaction to suppress the truth. They bribed the guards to spread a lie, prioritizing control over Christ’s victory.
Kingdom Reflection:
- Where does the modern business world pressure us to stay silent about our faith?
- Have we ever compromised truth for profit, reputation, or convenience?
"Whoever walks in integrity walks securely, but whoever takes crooked paths will be found out. (Proverbs 10:9, NIV)
2. The Kingdom Investor’s Response: Paying to Proclaim the Truth
While the world spends resources to suppress the Gospel, Kingdom Investors are called to fund its advance! The early church understood this; they gave sacrificially, even amid persecution, to spread the Good News.
Three Ways Kingdom Investors Can Proclaim the Resurrection:
- Invest in Gospel-Centered Businesses – Support ventures that align with biblical values.
- - Fund Missions & Ministry – Allocate resources to evangelism, discipleship, and mercy ministries.
- - Live with Bold Integrity – Let your business practices reflect Christ’s lordship.
"It is more blessed to give than to receive." (Acts 20:35, ESV)
3. The Ultimate ROI: Eternal Dividends
The world’s bribes fade, but Kingdom investments yield everlasting returns.
The resurrection proves:
- God honors faithfulness – Jesus’ victory was not bought; it was won by truth.
- Our work has purpose – Every ethical decision and Gospel investment echoes in eternity.
- The best is yet to come – The empty tomb guarantees our future hope!
Have a blessed week!
Fitsum Nigusse (Pastor)
EBN Ethiopia, Servant Leader
Scripture Focus:
"And when they had assembled with the elders and taken counsel, they gave a sufficient sum of money to the soldiers and said, 'Tell people, "His disciples came by night and stole Him away while we were asleep."’... So they took the money and did as they were directed." *(Matthew 28:12-15, ESV)*
1. The World’s Transaction: Paying to Hide the Truth
The religious leaders saw Jesus’ resurrection as a threat to their power and influence. Their response? A financial transaction to suppress the truth. They bribed the guards to spread a lie, prioritizing control over Christ’s victory.
Kingdom Reflection:
- Where does the modern business world pressure us to stay silent about our faith?
- Have we ever compromised truth for profit, reputation, or convenience?
"Whoever walks in integrity walks securely, but whoever takes crooked paths will be found out. (Proverbs 10:9, NIV)
2. The Kingdom Investor’s Response: Paying to Proclaim the Truth
While the world spends resources to suppress the Gospel, Kingdom Investors are called to fund its advance! The early church understood this; they gave sacrificially, even amid persecution, to spread the Good News.
Three Ways Kingdom Investors Can Proclaim the Resurrection:
- Invest in Gospel-Centered Businesses – Support ventures that align with biblical values.
- - Fund Missions & Ministry – Allocate resources to evangelism, discipleship, and mercy ministries.
- - Live with Bold Integrity – Let your business practices reflect Christ’s lordship.
"It is more blessed to give than to receive." (Acts 20:35, ESV)
3. The Ultimate ROI: Eternal Dividends
The world’s bribes fade, but Kingdom investments yield everlasting returns.
The resurrection proves:
- God honors faithfulness – Jesus’ victory was not bought; it was won by truth.
- Our work has purpose – Every ethical decision and Gospel investment echoes in eternity.
- The best is yet to come – The empty tomb guarantees our future hope!
Have a blessed week!
Fitsum Nigusse (Pastor)
EBN Ethiopia, Servant Leader
ሌሊቱን በልቅሶ ቢታደርም፣ በማለዳ ደስታ ይመጣል። (መዝሙር 30፥5)
ይህ “ሕማማት” የምንለው ሳምንት፣ የክርስቶስን ትንሣኤ ለማክበር ስንዘጋጅ ከትንሣኤው አስቀድሞ ያሳለፋቸውን የስቃይ ቀናት የምናስብበት ነው። ከትንሣኤው በፊት፣ የመቃብሩ ድንጋይ ከመንከባለሉ በፊት፣ በመስቀሉም ጭምር በፊት፣ ኢየሱስ በጌትሰማኒ የአትክልት ስፍራ ያሳለፈው ጭንቅ ነበር።
ኢየሱስ አሳልፎ ከመሰጠቱ አንድ ቀን በፊት፣ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ወደ ጌትሰማኒ ሄደ። ሊሆን ያለውን ነገር ስለሚያውቅ፣ ወድዶም ቢሆን ስለ ሰዎች ሁሉ ቤዛነት ሊጠጣት ያላትን ጽዋ መራርነት ስለሚያውቅ፣ ተጨንቆ ነበር። የሚመጣበት ክህደት፣ ክሱ፣ ስቃዩ፣ መከራው፣ ሊከፍለው ያለው ዋጋ ሁሉ ከፊት ለፊቱ ፍንትው ብሎ ይታየው ነበር። እንዲህ ሲል የጸለየው በዚህ ውስጥ ሆኖ ነው፤ “አባት ሆይ፤ ፈቃድህ ከሆነ፣ ይህችን ጽዋ ከእኔ ውሰድ፤ ነገር ግን የእኔ ፈቃድ ሳይሆን የአንተ ፈቃድ ይፈጸም” (ሉቃስ 22፥42)። ምንም እንኳ መልአክ ከሰማይ ተገልጦ ቢያበረታታውም ኢየሱስ፣ “እጅግ ተጨንቆም በብርቱ ይጸልይ ነበር፤ ላቡም እንደ ደም ነጠብጣብ ወደ ምድር ይፈስስ ነበር” ይላል (ቁጥር 44)። እንዲያ ባለ ስቃይ ውስጥ ሆኖ፣ በመከራ ጭንቅ ተይዞ፣ ያውም አንድም ኀጢአት የሌለበት እርሱ ለኀጥአን ቤዛ ሊሆን፣ የሚመጣውን ጽዋ ለመጠጣት መረጠ። የሰውን ልጅ ሊቤዥ ሥጋ ለብሶ የመጣበትን ዓላማ ለማሳካት፣ መንገዱን ከዳር ለማድረስ ቆረጠ።
ነገሩ ለንጽጽር የሰማይና የምድርን ያህል የራቀ ቢሆንም እንኳ፣ እንደ ክርስቲያን የቢዝነስ ሰዎች ይህ በጌትሰማኒ ኢየሱስ የተጋረጠበትን የውሳኔ ውጥረት የመሰለ ምርጫ ይጋረጥብናል። የእርሱን ጭንቅ ውቅያኖስ አድርገን ብንመስለው፣ እኛ የሚገጥመን ፈተና የጠብታ ያህል ይሆናል። እንዲያም ሆኖ የቆምንለትን ዓላማ በሐቀኝነት ይዘን እንቀጥል ወይስ ወደ ኋላ እንመለስ የሚል ጥያቄ በእያንዳንዱ ርምጃ ይጋረጥብናል። መንገዳችንን ከዳር ለማድረስ በሐቀኝነት መንገድ እንቀጥል፣ ወይስ አቋራጭ መውጫ እንጠቀም? የየራሳችን ትናንሽ “ጌትሰማኒዎች” ይገጥሙናል። ታግለን የጭንቁን ጊዜ አልፈን ወደ ክብር እንሻገር ወይስ ...?
ቢዝነስን በጽድቅ የመሥራት ፈተና
ባለው የአገራችን ሁኔታ፣ በሐቀኝነት ቢዝነስን ማከናወን ቀላል እንዳልሆነ የማይታበል እውነት ነው። ጭንቅ እየተሰማን፣ ብዙዎች እንደሚያደርጉት እግዚአብሔርን የማያስከብር “አቋራጭ መጠቀም እያሰኘን፣ ባስ ሲልም “ነገር ዓለሙን” ርግፍ አድርገን መተው እያማረን ወደየሥራችን የምንሰማራባቸው ቀኖች ይገጥሙናል። ምናልባት፣ “ይህችን ጽዋ ከእኔ ውሰድ” የምንልበት የውሳኔ ውጥረት በቢዝነስም በግልም ሕይወታችን ይመጣል።
ነገር ግን አልተተውንም። እርሱ አይተወንም። ማንም በማያውቅልን ጭንቅና ፈተና ውስጥ ሆነን እንኳ፣ ማንም የምናልፍበትን መከራና ስቃይ ባያውቅልን እንኳ፣ እርሱ መንገዳችንን ሁሉ ያውቃል። በጌትሰማኒ ኢየሱስን ያበረታው አምላክ እርሱ ያበረታናል። እርሱ እስከ ዓላማችን ፍጻሜ አብሮን ይጓዛል።
በመስቀል ውስጥ ማለፍ
የያዝነው የሕማማት ሳምንት የትንሣኤው መንገድ በመስቀሉ በኩል ታልፎ የሚገኝ መሆኑን የሚያሳስበን ነው። ይህ ባይሆን የትንሣኤው ድል ባልኖረ ነበር። እንደ አማኝ ያለን ሕይወትና ጉዞ ሁሉንም ሕይወታችንን የሚጠቀልል ነው። ቢዝነሳችንም ከዚህ ውጭ ሊሆን አይችልም። ጌታን መስቀላችንን ተሸክመን የመከተላችን ጉዞ፣ በቢዝነስም ጭምር ነው። የየራሳችን “የቢዝነስ መስቀል” ይኖረናል። በጽድቅና እግዚአብሔርን በማክበር እንሥራ እስካልን ድረስ፣ ይህ አይቀሬ ነው።
እንዲህ ባለ መልኩ መንገዳችንን እስከቀጠልን ድረስ፣ የሚገጥመን ፈተናና የጨለማ ጊዜ ለመጪው ብርሃን የምሥራች አብሳሪ ነው። የጌትሰማኒ ጭንቅ፣ የትንሣዔው ድል አብሳሪ ነው።
የአገራችን የቢዝነስ ንቅፍ፣ “የጌትሰማኒ መሪዎች” ያስፈልጉታል። እንዲህ ያሉ መሪዎች ጭንቅ ውስጥ ሲሆኑ ይጸልያሉ፤ ፈተና ሲገጥማቸው በሐቀኝነት ይጸናሉ፤ ከስሜታቸው አልፈው በእግዚአብሔር ይታመናሉ።
በዚህ የሕማማት ሳምንት፣ ከጭንቁ በስቲያ ያለውን ትንሣኤ እያሰብን የምንበረታበት እንዲሆን እግዚአብሔር ይርዳን።
ተባረኩ!
(አዲስ አሰፋ)



